በየደረጃው ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ወቅታዊ ልማታዊ ስራዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በመፈጸም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
በየደረጃው ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ወቅታዊ ልማታዊ ስራዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በመፈጸም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
‎
‎ነሀሴ 5/2018 የሳንኩራ ኮሙኒኬሽን
‎
‎በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ የማህበረሰቡን ሁሉ አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ወቅታዊ ተግባራትን መነሻ ያደረገ የግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡
‎
‎የወረዳ አመራር አካላትን በማሳተፍ የተካሄደው የግምገማ መድረክ ፤ በወረዳ ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ወቅታዊ ተግባራት አጠቃላይ አፈጻጸም ምን ይሚመስላል የሚለውን በማየት የአፈጻጸም ጉድለት የተስተዋለባቸው መዋቅሮች ከጉድለታቸው መውጣት እንዲችሉ በማስቻል በየዘርፉ ታቅደው እየተሰሩ ያሉ ወረዳዊ ተግባራትን ውጤታማ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡
‎
‎በመድረኩ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ወቅታዊ ተግባራት የአተገባበር ሂደትና ዝርዝር አፈጻጸሞች መነሻ ያደረገ ግምገማ ተካሂዷል፡፡
‎
‎ወቅታዊ ወረዳዊ ተግባራትን ለመገምገም የተካሄደውን የግምገማ መድረክ በሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ እና በሳንኩራ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ ሰልማን የተመራ ነው፡፡
‎
‎አሁን ላይ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ወቅታዊ ተግባራት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮነሚያዊ ተጠቃሚነት ባረረጋገጥ መልኩ ተግባራዊ መሆን እንዲችሉ አመራሩ በላቀ ቁርጠኝነት መፈጸም እንደሚገባ በአጽንኦት አስቀምጧል፡፡
‎
‎ ወቅታዊ ተግባራት ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ የገመገመው መድረኩ በሁሉም ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና በአሰራር ሂደት የተስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም ከሁሉም አመራር የሚጠበቅ መሆኑን አመላክቷል ፡፡
‎
‎
‎‎ወቅታዊ ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ዘላቂና ሁሉ አቀፍ ልማታዊ ለውጦች መመዝገብ እንዲችሉ በሀላፊነት መስራት እንደሚገባ በመድረኩ ማጠቃለያ ተመላክቷል፡፡
‎
‎መንግስት የዜጎችን ሁለንተዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በከተማ ልማት ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ ‎ማህበራዊ የልማት ዘርፎችን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ሁሉ አቀፍ የልማት ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ስለመሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
‎