"ሁለንተናዊ ብልፅግና ለኢትዮጵያ ልዕልና"

የሳንኩራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

የሳንኩራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻ

በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት

በ2018 ዓመታዊ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

የወሀ ፕሮጀክት የምረቃ ፕሮግራም

የሳንኩራ ወረዳ በፌድራል መንግስት የተሰራ 11 ቀበሌን ተደረሽ የሚየደርግ የCRw የወሀ ፕሮጀክት የምረቃ ፕሮግራም በክልሉ ፕሬዝደንት በዶክተር እንደሻው ጠሰዉ እነ በፌዴራል ውሀና ኤነርጂ ሚንስቴር ድኤታ በአምባሳደር አስፋው ዲንገሞ ዶ/ር የተመረቀበት መድረክ ።

የፕሮጀክት ምረቃ

የሳንኩራ ወረዳ የፖልስ ማዕከል ግንባታ የምረቃ ፕሮግራም ስመረቅ

የሰንጋ ስጦታ ስደረግ

በምርጫ ወቅት ባለድርሻ አካለት በመየዝ ለአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የሰንጋ ስጦታ ስደረግ

የሰንጋ ስጦታ ስደረግ

በምርጫ ወቅት ባለድርሻ አካለት በመየዝ ለአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የሰንጋ ስጦታ ስደረግ

የሳንኩራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አበዱልፈታ ሰልማን መልዕክት

Mr. Abdufeta Selman Head of Sankura PP ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ውብ ተምሳሌት፣ የተለያዩ ማንነቶች፣ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና አመለካከቶች በአንድነት የደመቁባት ታላቅ ሀገር ናት። የሕዝቦቿን ልዩነት ወደ ጥንካሬና ውበት በመቀየር፣ በመከባበር፣ በመቻቻልና በመተሳሰብ ለዘመናት የኖረች ሀገር ናት። ዜጎቿም ውድ ሕይወታቸውን በመስዋዕትነት በመክፈል የሀገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት አስከብረው ለትውልድ አስረክበዋል።
ነገር ግን ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተፈጠሩ የተዛቡ ትረካዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች ይህንን የጋራ እውነታችንን ለመሸርሸር ሞክረዋል። አንዳንድ ኃይሎችም አባቶቻችን የሀገር ምሰሶ ያደረጓቸውን እሴቶች የጥንካሬ ምንጭ ሳይሆን የድክመት ምንጭ ለማድረግ ሲሰሩ ቆይተዋል።
የሀገራዊ ለውጡ ፈንጣቂ የሆነው የብልፅግና ፓርቲ ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በዘላቂነት መፈወስ የሚቻለው በአገራዊ አንድነት፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ ውስጥ ብቻ እንደሆነ በፅኑ ያምናል። ለዚህም ነው አገራዊ አንድነታችንን በሕግ፣ በአሠራርና በተቋም ደረጃ የትኩረታችን ማዕከል ያደረግነው።
በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ የሳንኩራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በወረዳው ሕዝብ የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ሳንኩራ ወረዳ የሰላም፣ የአንድነት፣ የልማትና የምርታማነት ማዕከል እንደመሆኗ፣ በተለያዩ ዘርፎች የሚመዘገቡ ውጤቶች የወረዳውን ሕዝብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል፣ ልማትን ለማፋጠንና የብልፅግና ጉዟችንን ለማጠናከር የሚያበረክቱ ናቸው።
ባለፉት ዓመታት በሳንኩራ ወረዳ የሰላምና የመረጋጋት አየርን በማጠናከር፣ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የመሠረተ ልማትና የማህበራዊ ልማት ስራዎችን በማስፋፋት፣ የሕዝብና የመንግስት ትስስርን በማጠናከር እንዲሁም የወጣቶችና የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገብን ነው። የሳንኩራ ወረዳ የብልፅግና አሻራም በተጨባጭ እየጎላ መጥቷል።
እርግጥ ነው፣ በጉዟችን ላይ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። ሆኖም እኛ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ፣ አቅማችንን ወደ ላቀ ውጤት፣ ተግዳሮቶችንም ወደ ታላቅ ስኬት በመቀየር፣ በመተሳሰብና በወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ውድ የሆነችውን ሳንኩራ ወረዳን፣ የወረዳውን ሕዝብና ታላቋን ኢትዮጵያ ከፍ ለማድረግ በፅናት ወደፊት ተጉዘናል፤ ጉዟችንንም እንቀጥላለን!
በሳንኩራ ወረዳ በየደረጃው የምትገኙ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መላው የወረዳችን ማህበረሰብ፤ የውስጥ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር፣ ድህነትን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትንና ሙስናን በቆራጥነት በመታገል፣ የድካማችን ማማና የልፋታችን ውጤት የሆነውን ሁሉን አቀፍ ብልፅግና ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ትጋትና በተቀናጀ ተሳትፎ ነው።
በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የሳንኩራ ወረዳ ነዋሪዎች እንደ ሁልጊዜው የጽናታችን አለኝታና የጉዟችን ደጋፊ ሆናችሁ ከጎናችን እንደምትቆሙ ሙሉ እምነት አለን።
በመጨረሻም፣ ለዴሞክራሲያችን መጎልበት የማይተካ ሚና ያላችሁ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለሳንኩራ ወረዳ፣ ለአካባቢው ሕዝብና ለታላቋ ኢትዮጵያ ብልፅግና ሲባል በትብብርና በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ።
   ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ ፍቅርና ልፋት ትበለፅጋለች!
                                አመሰግናለሁ!
 

የቅርብ ጊዜ ዜና| Latest News

የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።

የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።

አምልጦዎት ይሆን |You May Have Missed

ሚዲያ እና ገጽ| Our Media

አጋሮቻችን I Our Partner